ኢትዮ ሶከር ዞን 4-5-1

ኢትዮ ሶከር ዞን 4-5-1 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኢትዮ ሶከር ዞን 4-5-1, Arbaminch gamo gofa, Arba Minch'.

አሻጋሪ እንጂ ተሻጋሪ አይደለምን ?አንድነት አዳነ ፦ በየትኛውም የእግር ኳስ ክለብ ውስጥ እንደምሰሶ እና መሰረት ተደርጎ ሊኖር የሚገባው ጀብደኛ ኳሰኛ ነው።በአርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ክለ...
30/08/2026

አሻጋሪ እንጂ ተሻጋሪ አይደለምን ?

አንድነት አዳነ ፦ በየትኛውም የእግር ኳስ ክለብ ውስጥ እንደምሰሶ እና መሰረት ተደርጎ ሊኖር የሚገባው ጀብደኛ ኳሰኛ ነው።

በአርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ታላላቅ ታሪኮች ውስጥ አብሪ ኮከብ በመሆን ፡ የአንድን ክለብ Spirit ጠባቂ ደጀን በመሆን ደረጃ ታላቅ ሰው ነው።

2ት ጊዜ አርባምንጭ ከነማ ወደ ፕ/ሊጉ ያሳደገ ፤ እንዲሁም ጋሞ ጨንቻን ለመጀመርያ ጊዜ ዘንድሮ ወደ ፕ/ሊጉ በመቀላቀል ደረጃ ከፍተኛውን ድርሻ ወሳጅ ሰው ነው።

(ማንጋላ-ዛምቦ) የብረት ምሰሶ 👏

ሰባተኛው ፍልሚያ በረቢቂ Rebik) አሸናፊነት ተጠናቀቀ!ኢትዮጵያ ድቡብ ሱዳንን አሸነፈችበዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው የ ኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ምሽት፣ በዕለቱ ሰባተ...
27/08/2026

ሰባተኛው ፍልሚያ በረቢቂ Rebik) አሸናፊነት ተጠናቀቀ!

ኢትዮጵያ ድቡብ ሱዳንን አሸነፈች

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው የ ኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ምሽት፣ በዕለቱ ሰባተኛ ፍልሚያ በሙአይ ታይ (Muay Thai Match) ዘርፍ በኢትዮጵያዊው ተዋጊ በረቢቂ (Rebik) እና በደቡብ ሱዳናዊው ተዋጊ ስቲፈን (Stephen) መካከል የተደረገው ዓለም አቀፋዊ ፍልሚያ በይፋ ፍጻሜ አግኝቷል።

በከፍተኛ ቴክኒክ፣ ብቃትና ወኔ በተሞላው በዚህ ግጥሚያ ተዋጊ ረቢክ ተጋጣሚውን ስቲፈንን በማሸነፍ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ሌላኛውን ደማቅ ድል አስመዝግቧል!

እንኳን ደስ አለህ ረቢቂ!

ላሳየኸው አስደናቂ የሙአይ ታይ ብቃትና የድል ወኔ እንኳን አበቃህ!

ቀጣይ የምሽቱ የፍልሚያ ውድድሮች በደመቀ ሁኔታ ይቀጥላሉ። ለተዋጊዎቻችን መልካም እድል እንመኛለን!

"ለድንግል ማሪያም ልጅ ምስጋና አቀርባለሁ.....Stay humble .....እናቴ እወድሻለሁ አንድ ቀን አሳርፍሻለሁ ታገሽኝ"  አብርሀም ከድሉ በኋላ🗣
27/08/2026

"ለድንግል ማሪያም ልጅ ምስጋና አቀርባለሁ.....Stay humble .....እናቴ እወድሻለሁ አንድ ቀን አሳርፍሻለሁ ታገሽኝ"

አብርሀም ከድሉ በኋላ🗣

እልፍ ጀግኖችን ለሀገር ያበረከተች፥ በአዕላፍ ልጆችዋ ዛሬም ድረስ የእግር ኳስ ተልዕኮዋ ሳይገታባት በኳስ ረሀብ ለተጠቁ ነዋሪዎችዋ ማስታገሻቸው የሆነችው Arbaminch ከተማ ወደ ቀድሞ ከፍ...
25/08/2026

እልፍ ጀግኖችን ለሀገር ያበረከተች፥ በአዕላፍ ልጆችዋ ዛሬም ድረስ የእግር ኳስ ተልዕኮዋ ሳይገታባት በኳስ ረሀብ ለተጠቁ ነዋሪዎችዋ ማስታገሻቸው የሆነችው Arbaminch ከተማ ወደ ቀድሞ ከፍታዋ ለመመለስ በሁሉም ሴክተሮች Reform ከጀመረች ሰነባብታለች።
‎
‎በይበልጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት ክለባችን አርባ ምንጭ ከነማ የበላይ አካላት በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ላይ ለሚገኙ ቡድኖቹ የአሰልጣኝ ቅጥር እየፈፀሙ ይገኛሉ።
‎
‎ነገር ግን ከ 10 ዓመታት በላይ በራስ ተነሳሽነት ታዳጊዎች ላይ የሚሰራ ጊዜውን ገንዘቡን አቅሙን ሰውቶ ለእረጅም አመታት ስያገለግል የቆየ ግለሰብ መዘንጋቱ እጅግ ያሳዝናል።
‎
‎ ወይም አልቦ አቢቲ የተለያዩ የስልጠና ኮርሶችን እየወሰደ በትልቅ ራዕይ እየተጓዘ የሚገኝ የዘመናችን ጀግና ወጣት እንዴት ሊዘነጋ ቻለ?
‎
‎እውነት ይሄ ልጅ ለዚህ ቦታ አይመጥንም? በከተማው ታዳጊዎች ላይ ላለፉት ጥቂት ለማይባሉ ዓመታት ለሰራው ስራ ሽልማቱ ይሄ ነው?
‎
‎መርህ የሌለበት ህይወት ስኬት አይጎበኘውምና ክለቡን የመርህ ( principle oriented ) እንዲሆን ሁሌም እንታገላለን።
‎
‎Arbaminch Kenema
‎

🚨 ፖል ፖግባ ገዢ ለማግኘት ከተቸገረ በኋላ የቅንጦት ቼሻየር መኖሪያ ቤቱን ዋጋ ከ3.95 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ 3.5 ሚሊዮን ፓውንድ ቀንሷል። 🏡💰ባለ አምስት መኝታ ቤት ሲሆን የቤት ውስጥ የ...
25/08/2026

🚨 ፖል ፖግባ ገዢ ለማግኘት ከተቸገረ በኋላ የቅንጦት ቼሻየር መኖሪያ ቤቱን ዋጋ ከ3.95 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ 3.5 ሚሊዮን ፓውንድ ቀንሷል። 🏡💰

ባለ አምስት መኝታ ቤት ሲሆን የቤት ውስጥ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የግል ሲኒማ ቤት፣ ጂምና የህክምና ክፍል አለው። 😮‍💨⚽

  💪👉ማንም ሰው በህይወቱ ብዙ አይነት ፈተናዎች ይገጥሙታል ነገር ግን እነዛን ፈተናዎች ተቋቁሞ አልፎ ዳግም ህይወትን ለማስተካከል እንደሚጥር ሰው ጀግና የለም።👉ከትልቁ ሊግ እስከ መጨረሻው ...
24/08/2026

💪
👉ማንም ሰው በህይወቱ ብዙ አይነት ፈተናዎች ይገጥሙታል ነገር ግን እነዛን ፈተናዎች ተቋቁሞ አልፎ ዳግም ህይወትን ለማስተካከል እንደሚጥር ሰው ጀግና የለም።

👉ከትልቁ ሊግ እስከ መጨረሻው የሃገሪቱ ሊግ በደንብ ታውቀዋለህ የግድ ስላንተ ለመፃፍ ዘመድ ወይም ጓደኛ መሆን አይጠበቅብንም (ቀመጮ) ዘንድሮ በልማት ካፕ ያየነውን አቅምህን በድጋሚ በከተማው ተወካይ ቡድን ላይ አሳየን ስላንተ እጅግ ደስተኛ ነኝ የነበረህን ይዘት ሳትቀይር ዳግም በከተማው ክለብ ላይ ብናይህ በጣም ደስተኞች ነን አንተ የጥረት ሰው🙏🙏🙏🙏🙏

እዉነት ለመናገር ከተማችን በእግርኳስ ዙሪያ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጣም አስደስቶኛል ይህም ካለፈዉ ስህተቶች ተምሮዉ በዚሀ በአጭር ግዜ ዉስጥ ወደ ለዉጥ መምጣቱን ወድጄዋለሁ ከተማችን አ...
24/08/2026

እዉነት ለመናገር ከተማችን በእግርኳስ ዙሪያ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጣም አስደስቶኛል

ይህም ካለፈዉ ስህተቶች ተምሮዉ በዚሀ በአጭር ግዜ ዉስጥ ወደ ለዉጥ መምጣቱን ወድጄዋለሁ

ከተማችን አይደሉም ለአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ ይቅርና ለመላው ኢትዮጵያ ላሉ ክለቦች የሚሆን ጥራትን ከችሎታ ጥንካሬን ከጥሩ ባህሪ ጋር ያለችው የዉብ እግርኳስ መፈለቅያ መሆኖ የሚታወቅ ሃቅ ነው

ባለፈው 10 አመታት ዉስጥ ከከነማዉ ተስፋ ቡድን አንስቶ በተለያዬ የሀገራችን ክለቦች ዉስጥ በወጥ እና በተለያዩ ቦታዋች መጫወት የሚች ለትኛዉ አሰልጣኝ ተመራጭነት ፀባዬሰናይ ባህሪ ያለው ተጫዋች ነው

በዘንድሮው በልማት ኳፕ ውድድር 02 ሰፈር አሸናፊ ካደጉት መሀል አንድ እና ምርጡን የዉድድር ዘመን ማሳለፍ ስለ ቻለ ተጫዋች ለማዉራት ወደድኩ Alazar tesfaye

# 2015/2016 ፈደራል ፖሊስ

#2017 አምቦ ከተማ

# 2018 ልደታ ክፍለ ከተማ አመቱን ሙሉ በወጥ የጫወታ ብቃት በመጫወት ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ ከቻሉት መሐከል አንድ ነው

ከተማ ቀጣይ በሚኖረ የዉድድር አመት ላይ ይህንን ልጅ የክለቡ አንዱ አካል ቢያደርጉት በጣም ምኞቴ ነው የቤቱ አካዳሚ ዉጤት እንደመሆኑ መጠን

✍️ ተሙ ጃ ሮክ

ከፍተኛ ሊጉን እንደ እጁ መዳፍ የሚያውቀው መስመረኛ!  ሁለገብ ተጫዋች ሲሆን መደበኛ ቦታው የመስመር ተከላካይ ነው። ነገር ግን በሜዳው ላይ ሁሉም ቦታ እየተገኘ የሁሉንም ስራ በደንብ የሚሰራ...
24/08/2026

ከፍተኛ ሊጉን እንደ እጁ መዳፍ የሚያውቀው መስመረኛ!

ሁለገብ ተጫዋች ሲሆን መደበኛ ቦታው የመስመር ተከላካይ ነው። ነገር ግን በሜዳው ላይ ሁሉም ቦታ እየተገኘ የሁሉንም ስራ በደንብ የሚሰራ ሁለገብ ተጫዋች ነው።

የቀድሞ ሺንሺቾ ፣ወራቤ፣ባቱ፣ጋሞ ጬንቻ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን አመት ከቤንች ማጂ ቡና ጋር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

Science Bacteria ሁሉም ቦታ ለይ ይገኛል ይላልና ይሄን ልጅ Amanuel Bacteria ብንልስ
ቆይ ስንቶቻችሁ ናችሁ አማኑኤል ያለው የጎል መጠን ከፍተኛ ሊጉ ላይ ጨራሽ ከተባሉ አጥቂዎች እና ከፍተኛ ገንዘብ ከወጣባቸው አጥቂ አማካይ ከሆኑ ተጫዋቾች በላይ ብዙ ጎል ማስቆጠሩን ብዙ ለግብ የሆኑ ኳሶቹን ማቀበሉን ምታውቁት 👌

የእሱን የጨዋታ position ይሄ ነው ብሎ መናገር ይከብዳል ፥ ምክንያቱም እሱ ሁሉም ቦታ ላይ አለ ብቻ ልጁ ይችላል። በመከላከል ሰዓት 1ለ1 በሆኑ ክስተቶች ላይ ሲቸገር አይታይም።👏

በዚሁ አቋሙ በከፍተኛ ሊጉ ከታዩ ምርጥ የመስመር ተከላካይ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን እምቅ አቅም እና ችሎታ ያለው ልጅ ነው ::

(ጩቴ) መልካሙ ይግጠምህ 👏

✍️ ቤቾ የእናቱ ልጅ

አርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ም/ል አሰልጣኝ ሿሟል!ከዚህ ቀደም ከፋ ቡና፣ቡሌ ሆራ፣ሀዲያ ሌሞ፣እንጅባራ ከተማ፣ዱራሜ ከተማ እና አክሱም ከተማን ማሰልጠን የቻለው እና ዱራሜ ከነማን ወደ ...
24/08/2026

አርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ም/ል አሰልጣኝ ሿሟል!

ከዚህ ቀደም ከፋ ቡና፣ቡሌ ሆራ፣ሀዲያ ሌሞ፣እንጅባራ ከተማ፣ዱራሜ ከተማ እና አክሱም ከተማን ማሰልጠን የቻለው እና ዱራሜ ከነማን ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማሳደግ የቻለው አሰልጣኙ አዲሱ ዶይሳ (ወዲዴ) የአርባምንጭ ከነማ ም/ል አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል።

"ኢትዮጵያ ቡና አልፈለገኝም'' -አቡበከር ናስር "እኔ ኢትዮጵያ ቡናን አልከዳሁም ራሴ ደውዬ አነጋግሬያለሁ ጥሩ ምላሽ አልሰጡኝም እኔን ትሪት ያደረጉበት መንገድ አሳዝኖኛል ኢትዮጵያ ቡና አል...
24/08/2026

"ኢትዮጵያ ቡና አልፈለገኝም'' -አቡበከር ናስር

"እኔ ኢትዮጵያ ቡናን አልከዳሁም ራሴ ደውዬ አነጋግሬያለሁ ጥሩ ምላሽ አልሰጡኝም

እኔን ትሪት ያደረጉበት መንገድ አሳዝኖኛል ኢትዮጵያ ቡና አልፈለገኝም

ኢትዮጵያ ቡና ላይ ጎል ካስቆጠርኩ ደስታዬን አልገልፅም"

Address

Arbaminch Gamo Gofa
Arba Minch'

Telephone

+251916990065

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ሶከር ዞን 4-5-1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኢትዮ ሶከር ዞን 4-5-1:

Shortcuts

Share