የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS Perform procurement of public organization common user items and nationally strategic utilities; render efficient and effective property disposal service;

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ሐምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሲቋቋም ዓላማዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን የመንግስት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡

በአገልግሎቱ ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው*****ዜና፣መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ተቋማዊ አሠራሩን ለማሻሻልና...
18/09/2026

በአገልግሎቱ ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው
*****
ዜና፣መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ተቋማዊ አሠራሩን ለማሻሻልና የሥራ ቅልጥፍናን ለማሳደግ በአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ በተዘጋጁ ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ የሠራተኞችን ግብዓትና አስተያየት ለማሰባሰብ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በአገልግሎቱ የግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም፣ መድረኩ ረቂቅ ማንዋሎችን በጥልቀት በመፈተሽ ክፍተቶችን ለይቶ የሠራተኞችን ግብዓት በማካተት ማንዋሎቹን የበለጠ ግልጽና ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመድረኩ የግዥ፣ የውል አስተዳደር፣ የንብረት ማስወገድና የገበያ ጥናት ረቂቅ የውስጥ አሰራር ስርዓቶች (ማንዋሎች) ቀርበው ግብዓት የሚሰባሰብ ይሆናል ።
በመድረኩ የአገልግሎቱን ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያምን ጨምሮ፡ ስራ አስፈፃሚዎችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች አንዲሁም በማንዋል ዝግጅቱ የተሳተፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ምሁራን እና ከገንዘብ ሚኒስቴር የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፋ ይገኛሉ።

10/09/2026
የመንግስት ግዥ አገልግሎት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሄደ******************ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገ...
09/09/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሄደ
******************
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት “ጳጉሜ 04 የኅብር ቀን” ምክንያት በማድረግ 26 ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ የአገልግሎቱ ሠራተኞቹ እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ለሚኖሩ 9 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ለእያንዳንዳቸው የዓመት በዓል መዋያ የሚሆን 5 ሊትር ዘይትና 5 ኪሎ ግራም ዱቄት ድጋፍ ተደርጓል። የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ በማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን እንደ ተቋማዊ እሴት በመያዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህል በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በአውሮፓ ሕብረት ድጋፍ በተዘጋጁ ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ የሠራተኞች ግብዓት ማሰባሰቢያ ወርክሾፕ ተካሄደ*********************ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 03 ቀን 201...
08/09/2026

በአውሮፓ ሕብረት ድጋፍ በተዘጋጁ ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ የሠራተኞች ግብዓት ማሰባሰቢያ ወርክሾፕ ተካሄደ
*********************
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት፣ የሥራ አፈጻጸሙን ለማሻሻል፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲሁም የሥራ ቅልጥፍናን ለማሳደግ የማሻሻያና የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በዚህ ማዕቀፍ አገልግሎቱ የ2019–2023 ዓ.ም የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀትና በሥራ አመራር ቦርዱ በማፀደቅ ወደ ትግበራ ለማስገባት ዝግጅት ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም ዋና ዋና የሥራ ሂደቶችን ይበልጥ ለማሳለጥና የተቀላጠፈ ተቋማዊ አሠራር ለመፍጠር፣ ከአውሮፓ ሕብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተዘጋጁ የውስጥ አሠራር ረቂቅ ማንዋሎች ላይ የሠራተኞችን ግብዓትና አስተያየት ለማሰባሰብ የተዘጋጀ ወርክሾፕ ተካሄዷል።
በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ የተገኙት የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፣ የወርክሾፑ ዋና ዓላማ በዋና ዋና የሥራ ሂደቶች ላይ የተዘጋጁትን ረቂቅ ማንዋሎች በጥልቀት በመፈተሽ ያሉ ክፍተቶችንና ግልጽ ያልሆኑ አሠራሮችን መለየት እንዲሁም የሠራተኞችን አስተያየትና ግብዓት በማካተት ማንዋሎቹን ይበልጥ ግልጽ፣ ተግባራዊና ተቋማዊ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ የተዘጋጁት ማንዋሎች የሥራ ሂደቶችን በግልጽነት፣ በወጥነትና በተቋማዊ አሠራር ለመምራት የሚያግዙ ወሳኝ የሥራ መሣሪያዎች መሆናቸውን ጠቁመው፣ ማንዋሎቹ የሠራተኞችን የሥራ ልምድና ተጨባጭ ግብዓት አካትተው እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሠራተኛ በነጻነትና በባለቤትነት ስሜት አስተያየትና ግብዓት በመስጠት በንቃት እንዲሳተፍ አሳስበዋል።
ክቡር አቶ አስማረ በማንዋል ዝግጅቱ ለተሳተፉ የአገልግሎቱ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ማንዋሉ እንዲዘጋጅ የገንዘብ ድጋፍ ላደረገው የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክት ጽ/ቤት እንዲሁም በዝግጅቱ ሂደት ሙያዊ ትብብር ላደረጉ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አማካሪዎችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በወርክሾፑ በተዘጋጁት የግዥ፣ የውል አስተዳደር፣ የንብረት ማስወገድ እና የገበያ ጥናት ረቂቅ የውስጥ አሠራር ማንዋሎች ላይ በየዘርፉ በሥራ መሪዎች ገለጻ ተደርጎ፣ ሰፊ ውይይት በማካሄድ ከሠራተኞች አስተያየትና ግብዓት ተሰብስቧል።
በተጨማሪም በዕለቱ ለአገልግሎቱ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ በተለይም ለጥበቃ፣ ለጽዳት፣ ለቢሮ ረዳትና ለሹፌሮች ከሥራቸው ባህሪ ጋር ተያያዥ የሆነ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በመሰረታዊ አገልግሎቶች ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ሞላ ተሰጥቷል።
ይህም በአገልግሎቱ እየተካሄደ ያለው ማሻሻያና ሪፎርም ሁሉንም ሠራተኛ ያማከለ፣ የሠራተኞችን አቅም የሚያጎለብትና የተቋሙን አፈጻጸም የሚያሻሽል እንዲሆን እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል።
በመጨረሻም የአገልግሎቱ የግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም የዕለቱን መርሐ ግብር በማጠቃለል፣ ከሠራተኞች ግብዓትና አስተያየት ለመሰብሰብ የተዘጋጀው ወርክሾፕ የማንዋሎቹን ጥራትና ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም በወርክሾፑ የተሰጡ አስተያየቶችና ግብዓቶች በማካተት ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ግልጽና ተግባራዊ የአሠራር ማንዋሎችን በማዘጋጀት፣ ሥራዎችን በተደራጀና በወጥነት ለመምራት የሚያግዙ ዘላቂ የሥራ መመሪያዎች እንዲሆኑ ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

08/09/2026

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ጨረታ ተከፈተ
**********************
ዜና፣አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የ8 መ/ቤቶች የሆኑ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ጨረታው በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአገልግሎቱ አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አከናወነ*******************ትናንት ነሐሴ 29 እና ዛሬ፣ ነሐሴ 30 ቀን ...
05/09/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አከናወነ
*******************
ትናንት ነሐሴ 29 እና ዛሬ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በመገኘት የተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን አከናወነዋል፡፡
አመራሮችና ሠራተኞች በትናንት መርሐ ግብር ከዞኑና ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት በዞኑ በሀሩካ ወረዳ አንድዶ ቀበሌ የሚገነባውን ዘመናዊ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት አከናውነዋል፡፡
ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሐ ግብር ደግሞ አዋሽ-7 ከተማ ላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን አልፈው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ 200 ለሚሆኑ ተማሪዎች/ወጣቶች በአገልግሎቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢቲሳ ደሜ ካላቸው የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ተሞክሮ በመነሳት የልምድ ልውውጥ፣ ማበረታቻ እና ለቀጣይ የትምህርት ዝግጅታቸው የሚረዳ የማነቃቂያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከ1000 በላይ የሚሆን በመስኖ የሚለማ የሙዝ ችግኝ ተከላ የተከናወነ ሲሆን ከ500 ሺ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን በዞኑ በገራአሎ ወረዳ ለሚገኙ ለ150 የአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ልጆች ለሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ልማት የራሳቸውን አሻራም አሳርፈዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፣ በዕለቱ የተከናወኑት ተግባራት ለመጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋ ከመገንባትና አሻራ ከማሳረፍ ባሻገር፣ አብሮነትንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩና የአገልግሎቱን ማኅበራዊ ኃላፊነት በተግባር የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸው፣ መሰል የበጎ ሥራ ባህል በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የገቢ ረሱ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሁሴን መሀመድ በበኩላቸው፣ የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት የክረምት በጎ ሥራውን በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች መስራቱ የሚያበረታታና የአብሮነት ባህልን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው፣ ለተደረገላቸው ድጋፍ እና ለተከናወነው የበጎ ተግባር ስራ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሄደ***************ዛሬ፣ አርብ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም...
04/09/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሄደ
***************
ዛሬ፣ አርብ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በመገኘት የተለያዩ የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎችን አስጀምረዋል።
በተለይም በክልሉ ገቢ ረሱ ዞን በሀሩካ ወረዳ የሚገነባውን ዘመናዊ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በልዩ ድምቀት ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ፣ ሁሩካ ወረዳ፣ ገርአሎ ወረዳ እና የአዋሽ 7 ከተማ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት የትምህርት ቤቱ ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፤ “የአፋር ሕዝብ በአገር ወዳድነቱ፣ በባህሉና በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ ታሪካዊ ሕዝብ ነው ያሉ ሲሆን፤ በሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ ባለው እና የሉሲ መገኛ በሆነው አፋር ክልል ተገኝተን ከእናንተ ጋር መሆናችን ለእኛ ታላቅ ደስታና ልዩ ክብር ነው በማለት” ለአፋር ህዝብ ያላቸውን ክብርና አድናቆት እንዲሁም የተሰማቸውን ልዩ ደስታ ገልጸዋል፡፡
ከፌዴራል መንግስት በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታው የሚከናወን መሆኑን ገልጸው፤ የትምህርት ቤቱ ግንባታ የሕፃናትን የመማሪያ ሁኔታ ከማሻሻል ባሻገር በአካባቢው የትምህርት ልማትን ለማጠናከር የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ አጽኖኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
በነገው ዕለትም ቀሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች በዞኑ በሌሎች ወረዳዎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የጋራ ተቋማዊ አቅጣጫን እና ወቅታዊነትን የሚያንፀባርቅ ሊሆን እንደሚገባ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ ገለፁ ።ዜና፣ አዳማ፣ ነሐሴ 26 ቀን...
01/09/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የጋራ ተቋማዊ አቅጣጫን እና ወቅታዊነትን የሚያንፀባርቅ ሊሆን እንደሚገባ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ ገለፁ ።
ዜና፣ አዳማ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዓመታዊ የስራ ዕቅድ ዝግጅት ወርክሾፕ በአዳማ እያካሄደ ይገኛል ።
በወርክሾፑ ላይ የተገኙት የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እንዳሉት አገልግሎቱ ቀደም ሲል የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አዘጋጅቶ እንደነበር ጠቁመው ፤ በአሁኑ ወቅት የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በስራ አመራር ቦርዱ በመፅደቁና ዓመታዊ ዕቅዱን ከስትራቴጂክ ዕቅዱ አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ጋር ማስማማትና ማስተሳሰር በማስፈለጉ ይህ ወርክሾፕ ተዘጋጅቷል ብለዋል ።
በመሆኑም ወርክሾፑ ዝርዝር ተግባራትን ለማሻሻል ብቻ ሳይሆን የስትራቴጂክ ቅድሚያዎችን ወደ ተጨባጭ ተግባርና ውጤቶች ለመተርጎም የሚያስችል ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሚዘጋጀው ዓመታዊ ዕቅድም የጋራ ተቋማዊ አቅጣጫን እና ወቅታዊነትን የሚያንፀባርቅ እንዲሆን ሁሉም በቅንነትና በግልፅነት ሊሳተፍ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
ወርክሾፑ በEU የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት አማካሪ በፓሜላ ማሬንዲ ( ዶ/ር) ቴክኒካል ድጋፍ እየተካሄደ ሲሆን ለቀጣይ 5 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
በመድረኩ የመንግስት ግዥ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ ከአገልግሎቱ የተውጣጡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS:

Shortcuts

Share