21/07/2026
" በደሞዝተኞች ላይ የሚጣለው ግብር ሊሻሻል ይገባል " - ፕራግማ ካፒታል
ደሞዝተኛው ማህበረሰብ ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚደርስበትን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ፣ መንግስት በደሞዝ ላይ የሚጥለውን የግብር መጠን ሊያሻሽል እንደሚገባ ፕራግማ ካፒታል የተሰኘው ድርጅት ገለጸ።
ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በደሞዝተኞች ላይ ከፍተኛ ግብር የምትጥል ሀገር መሆኗን አመልክቷል።
ከፍተኛ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከግብር ጫናው ጋር ተዳምሮ በደሞዝተኞች ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የገለጰው ድርጅቱ፣ መንግሥት የደሞዝ ግብር ስርዓቱን ሊያሻሽለው እንደሚገባ ጠቁሟል።
viaEthio FM